የቱሪዝም ቀን ከአርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል ጋር ተከብሯል::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ27/2017ዓ.ም-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብሮች ውስጥ አንዱ የቱሪዝም ቀን ሲሆን ፣ ሚያዚያ 27 የሚከበረውን 84ኛውን የኢትዮጵያ አርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ በሚገኘው ድንቅ የተፈጥሮ ሀይቅ “ሎማ ሀይቅ” ጉብኝት ተደርጓል:: ሎማ ሀይቅ ከሰመራ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 30ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ የሚገኝ ለጅኦቱሪዝም አመቺ የሆነ የተወሰነ ፍልውሃም ያለው ሀይቅ መሆኑን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምድር ትምህርት ቤት የሰጠን መረጃ ያመለክታል::
የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መካሄድ ጀምሯል።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ27/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት በተለያዩ መርሃግብሮች ዛሬ ተጀምሯል:: በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ዶ/ ር መሀመድ ኡስማን (የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት)፣ የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሀሚድ ዱላ (በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአፋር ክልል ባህል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ)፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት የተከፈተው የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በቅርቡ በድንገተኛ አደጋ በሞት ለተለየን ለወጣቱ የስፖርት ጋዜጠኛ ኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ) የህሊና ፀሎት ተደርጓል:: በተጨማሪም ኑር ሁሴን በስፖርቱ ዘርፍ በዩኒቨርሲቲው እግርኳስ ክለብ እና ለክልሉ ስፖርት እድገት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጾ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ሜዳ በስሙ ተሰይሟል:: ዛሬ በAdmin እና በCDA-Health College መካከል የተደረገው ጨዋታ አምና ዋንጫ በወሰደው Admin 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል:: በዛሬ ከሰአት መርሃ ግብር በAcademic Admin እና College of Engineering and Technology መካከል ጨዋታው የሚቀጥል ይሆናል::
The University Provides Thesis Training to Awash Center Postgraduate Students.
The University Provides Thesis Training to Awash Center Postgraduate Students. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለአዋሽ ማዕከል የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ጥናታዊ ፅሁፍ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ስልጠና ከሚያዚያ 24-26 ሰጥቷል። #Samara_University_4_May_2025 — Samara University has conducted a comprehensive training session focused on academic thesis preparation for its postgraduate students at the Awash Teaching Center. Held from May 2–4, 2025, the training aimed to equip postgraduate students with the necessary skills and guidance to successfully complete their thesis projects. Located 370 kilometers from the university’s main campus, the Awash Teaching Center was established as part of Samara University’s broader commitment to expanding educational access to the community. And also steadily extended its academic footprint operating teaching campuses in Worer, Bati, Aysaita, Chifra, and Abala, offering undergraduate and graduate programs.
ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ተከስቶ ለነበረው የፍየል ወረርሽኝ ምላሽ መስጠቱን ገለፀ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/23/2017 ዓ/ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ: የዱብቲ ወረዳ ማህበረሰብ በፍየሎች ላይ ሰሞኑን ለተከሰተው ወረርሽኝ አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለዩኒቨርሲቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከሚያዚያ 18 እስከ 21/2017 ዓ.ም የተንቀሳቃሽ ህክምና አገልግሎት መስጠቱ ተገልጿል:: ዩኒቨርሲቲው ጥያቄውን ተቀብሎ የሀኪሞች ቡድን በመላክ በጥናት ላይ የተመሰረተ ህክምና በሽዎች ለሚቆጠሩ ፍየሎች እና በጎች በዋድ ባዱራ፤ ቀበሌ 03 እና ሂናሌ ቀበሌዎች ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። የሀኪሞቹ ቡድን ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ በቦታው ሲደርሱ 3 ፍየሎች ሙተው 100 የሚሆኑት በከባዱ ታመው ተቅማጥ፣ሳል የአፍንጫ ፍሳሽ እና ሙቀት የሚታይባቸው ፍየሎች ማግኘታቸውንና ማከማቸውን እንድሁም የግንዛቤ ትምህርት መስጠታቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ባለሙያዎቹ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ገልፀው የሚከተሉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ለህብረተሰቡ አስተላልፈዋል:: * የህመም ምልክት ሲያዩ የታመሙትን ከጤናማዎቹ ለይቶ ማቆየት: በተናጥል መመገብ እና በቂ የውሃ መስጠት * አዲስ የሚገቡ ፍየሎችን ከመንጋው ጋር ሳይቀላቀሉ ለሁለት ሳምንታት ለይቶ መከታተል * እንስሳቱ የተለመዱ በሽታዎችን መከላከያ ክትባቶችን መውሰዳቸውን ማረጋገጥ * የበሽታ ስርጭትን ለመቀነስ መጠለያዎችን እና የምግብ እና የውሀ ቦታዎችን አዘውትሮ ማጽዳት:ንፅህናውን መከታተል * የተለዩ ክስተቶችን ሲያዩ በአፋጣኝ ለእንስሳት ህክምና ማእከል/ባለሙያ ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል:: #ማህበረሰቡንእናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ
“በጀመርነው የ1 ሚሊዮን ተምር ልማት ትልቁን የምርምር እና የምርት ማዕከል እውን እናደርጋለን” ዶ/ር መሐመድ ኡስማን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ለኢዜአ እንደገለጹት::
#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ_23_2017-“ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በቅርቡ በአይሳኢታ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ማዕከል በ2ሺ 500 ሄክታር መሬት ላይ በቀጣይ 3 አመታት የእንስሳት መኖ ያመርታል: ከ8-10 ባለው አመት ውስጥ ደግሞ 1 ሚሊዮን ተምር በማልማት በሀገራችን ትልቁን የምርት እና የምርምር ማዕከል እውን እናደርጋለን” ሲሉ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሐመድ ኡስማን ትናንት ለኢዜአ በሰጡት ቃለመጠይቅ ገልጸዋል:: ፕሬዚደንቱ እንደገለጹት የአይሳኢታ የተቀናጀ የግብርና ምርምር ማዕከል ካፒታል ፕሮጀክት ሙሉ በሙሉ ስራ ሲጀምር እንደ ሀገር በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረጉት ጥረቶችን በመደገፍ: በፆም ወቅት በሚሊዮን ዶላሮች ከውጪ የሚገባውን የቴምር ምርት በሀገር ውስጥ ምርት መተካት የሚያስችል እና ለብዙዎች የስራ እድልን የሚፈጥር ፕሮጀክት መሆኑን ገልጸዋል። አምና የተጀመረው ይህ ፕሮጀክት የአዋሽን ወንዝ ከ6 ኪሜ ርቀት ላይ የመጥለፍ ስራው የተገባደደ ሲሆን: ሌሎች የግብርና መሰረተ ልማቶች ከ70 በመቶ በላይ ተከናውኗል:: የተምር ምርት በአፋር ክልል አይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች በግለሰቦች እና በማህበራት ደረጃ ለብዙ አስርት አመታት እየተሰራበት ያለ ቢሆንም: በዘርፉ አንቱታን ያተረፉ አለም አቀፍ የምርምር ተቋማት እና ባለሀብቶች ጋር በመተባበር በምርምር እና በቴክኖሎጂ የታገዘ የተምር ግብርናን እውን ለማድረግ ከተደረጉ ጥረቶች ውስጥ : የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በ2015 ዓ.ም የተባበሩት አረብ ኢመሬት አምባሳደር በኢትዮጵያ መሀ ሳሌም አል-መህዲ ጋር ውይይት አድርገው ነበር: በተጨማሪም ከሞሮኮ:ሳኡድ አረቢያ:ኩዌይት ኤምባሲዎች ጋር የተጀመሩ ግንኙነቶች አሉ:: ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የሚገኝበት አፋር ክልል ለበርካታ የምስራቅ አፍሪካ: ኤሲያ እና አውሮፓ ሀገራት ስትራቴጅካዊ ቅርበት ስላለው: ለወጪ እና ገቢ ምርት የገቢያ ትስስር አመቺ መሆኑ እና ከታወቁት የቴምር አምራች ሀገራት ጋር ተቀራራቢ የአየር ንብረት ያለው : እንዲሁም ሰፊ መሬት እና አመቱን በሙሉ የሚፈስ የውሀ ሀብት መገኛ መሆኑ : ፕሮጀክቱ ተስፋ የሚጣልበት አድርጎታል:: በተጨማሪም በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልየታ መሰረት የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲ(University of Applied Science) ሆኖ መለየቱ እና የክልሉን ፀጋዎች ታሳቢ ያደረጉ የትኩረት መስኮች ማለትም ግብርና(የእፅዋት እና እንስሳት): ቱሪዝም እና ስነ-ምድር(ማዕድን) የተሰጡት በመሆኑ: የአይሳኢታ ግብርና ምርምር ማዕከል የተምር ፕሮጀክት የሀገራችንን የግብርና ታሪክ የሚቀይር እንደሚሆን ገልጸዋል:: ይህ ፕሮጀክት በ2018 መጨረሻ ላይ ሙሉ በሙሉ ወደ ስራ ሲገባ ከማስተማሪያ እና ምርምር ማእከልነቱ በተጨማሪ ከሚያገኘው የእንስሳት መኖ ምርት እና በዋናው የተምር ምርት አማካኝነት ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚሸጋገርበት ፕሮጀክት መሆኑም ተገልጿል:: ቴምር በተፈጥሮ ብዙ ጥቅሞችን የተቸረው ተወዳጅ ምግብ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ:: የግብርና ሚኒስቴር እንዲሁም የአፋር ክልል መንግስት የቴምር ምርትን ለማሳደግ በዩኒቨርሲቲው ብሎም በክሉ የነበሩና የተጀመሩ ጥረቶችን ለማጠናከር ትኩረት መስጠታቸው የሚመሰገን ነው:: በግብርና ሚኒስቴር እና በከሊፋ ዓለም ዓቀፍ የቴምር ልማትና ምርምር ተቋም የተፈረመውን የመግባቢያ ስምምነት ተከትሎ ከሚኒስቴር መስሪያቤቱ እና ከምርምር ተቋሙ የተውጣጣ ልኡክ በአፋር ክልል አይሳኢታና አፋምቦ ወረዳዎች ላይ እየተከናወነ ያለውን የቴምር ልማት የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የስራ ኀላፊዎች በተገኙበት የመስክ ምልከታ ማድረጋቸው ለጉዳዩ የተሰጠውን ትኩረት ያሳያል። መሀመድ አህመድ አበጋር #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈጻሚ.
The time has come to Ethiopia’s Date Palm Production Development.
#Samara_University_30April 2025-Following the discussion and MoU between Ethiopia and The United Arab Emirates (UAE) governments on Date Palm Production Development, today the team of UAE’s researchers and experts of date palm paid a visit to Afar Region Date Palm Farms. The team involved Dr. Efa Muleta(state minister of Agriculture), Dr. Mohammed Usman (Samara University President), Mr. Umer Nur Arba (Vice President of Afar National Regional State), Mr. Nur Tahir(A/N/R/S vice head of Office of the President), Mr. Usman Mohammed Humed (A/N/R/S Agriculture Bureau V/Head), Wolae Witika(A/N/R/S Irrigation and Law land Burea Head, Samara university College of Dry Land Agriculture Experts, Agriculture Bureau Experts. According to the Ministry of Agriculture, International Palm Festival will be organized in August 26-28/2025 in Ethiopia, probably in Afar, aimed at exchanging knowledge and technology and bringing together organizations engaged in palm production across the world. Samara University will take the research and development initiatives in collaboration with the National and Regional Agriculture Authorities and the UAE. The University has ongoing grand Date Palm Project at Aysaita Agricultural Research Center expected to plant 1million Date Palms on its 2500 hectare fertile research site. The MoU was signed by Minister of Agriculture, Girma Amente (PhD), and the Secretary General of Khalfa International Award for Date Palm and Agricultural Innovation of the United Arab Emirates, Abdelouahhab Zaid on 28 April 2025. #WeServetheCommunity! Mohammed Ahmed Abegar Yared Alemu Public Relations Executive
በዩኒቨርሲቲው የቤተ-ሙከራ/የተግባር ትምህርት ሳምንት ተካሂዷል::
#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ_18 ቀን 2017 ዓ.ም-በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ሁሉንም ኮሌጆች እና ትምህርት ቤቶች ያሳተፈ የቤተ-ሙከራ እና የመስክ-ምልከታ የተግባር ትምህርት ሳምንት ተካሂዷል::  የተግባር ልምምድ ሳምንቱ አላማ ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር እንዲሰሩ እድል መስጠት ሲሆን: ይህም የቡድን የንቅናቄ መንፈስን በማምጣት ከመደበኛው የቤተ-ሙከራ ክፍለ ጊዜ በተጨማሪ በተማሪዎች እና በቤተ-ሙከራ ባለሙያዎች መካከል በትብብር መስራትን: መጠየቅን እና ደጋግሞ የመሞከር ባህልን መፍጠር እንደሆነ ተገልጿል:: ይህ ተግባር በአመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ ተቋማዊ ባህል ሆኖ የሚቀጥል በመሆኑ የዩኒቨርሲቲውን የተግባር ዩኒቨርሲቲነት ሂደት(Transition to University of Applied Sciences) ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተለይ ኮሌጆች እና ት/ት ቤቶች: መምህራን:የቤተ ሙከራ ቴክኒካል ረዳቶች:ተማሪዎች ሁሉም በየደረጃው ለጉዳዩ የሚሰጠው ትኩረት እንዲጨምር ሚናው የጎላ ነው ተብሏል::
የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች (የማኔጅመንት አባላት) ጋር የማጠቃለያ ውይይት አደረገ።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/17/2017 ዓ/ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሚኒስቴር ሱፐርቪዥን ቡድን ለሁለት ቀናት ያደረገውን የውይይት እና የምልከታ መርሃግብር ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች (የማኔጅመንት አባላት) ጋር ባደረጉት የማጠቃለያ ውይይት እና ሪፖርት አጠናቀዋል። በትናንትናው እለት ከተማሪዎች ፣ ከመምህራን፣ ከአስተዳደር ሰራተኞች እና ከመካከለኛ አመራሮች ጋር በተናጠል ባደረጉት ውይይት የወሰዷቸውን ነጥቦች ፣ዛሬ ካደረጉት የተለያዩ የመሰረተ ልማቶች እና የስራ ክፍሎች የመስክ ምልከታ የያዟቸውን ነጥቦች አንድ ላይ አጠቃለው ከከፍተኛ አመራሩ ጋር ተወያይተዋል። በሁለቱ ቀናት ውይይቶች እና ምልከታዎች በተቋሙ እየተተገበሩ ያሉ የአስተዳደር ፣ የመማር ማስተማር ፣ የምርምር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ጉዳዮችን ከቁልፍ የአፈፃፀም አመልካቾች (KPI) አንፃር ጥንካሬዎችንና ክፍተቶችን በመለየት ገንቢ ውይይት አድርገዋል:: ልኡኩ በቆይታው በጥንካሬ የወሰዳቸውን አፈፃፀሞች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ: ማስተካከያ የሚፈልጉ ብሎ የለያቸውንና በዩኒቨርሲቲው ደረጃ መፈታት የሚችሉትን በትኩረት እንዲሰራባቸው: የትምህርት ሚኒስቴርን ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን ለሚኒስቴር መስሪያቤቱ እንደሚያቀርቡ አመልክተዋል:: በተለይም የመንግስትን ልዩ ትኩረትና ድጋፍ የሚፈልጉ የአካባቢው የሙቀት ሁኔታ ያገናዘበ የበጀት ድልድል እና የመብራት የሀይል አቅርቦት: የሀገር አቀፍ ፈተናዎች መርሃግብር እና ሌሎችንም ጥያቄዎች ለበላይ አካል እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል:: ዩኒቨርሲቲው ከተፈጥሮ ጋር እየታገለም ቢሆን አመራሩ በየደረጃው እና ሰራተኛው በመናበብ የሰሯቸው በርካታ ለሌሎችም ተሞክሮ የሚሆኑ አሰራሮችን እና ተቋማዊ ባህሎችን እንደተገነዘቡ ገልጸዋል:: በመጨረሻም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን በልኡኩ እና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ መካከል ለተደረገው ነፃ ውይይት እና የመስክ ምልከታ መሳካት የዩኒቨርሲቲውን ማህበረሰብ እና ልኡኩን አመስግነው: ይህም ጥንካሬዎቻችንን በማስቀጠሉ ረገድ እና ክፍተቶቻችን ለይትን ለመሙላት : በተለይም የቁልፍ ተግባራትን ትኩረት ሰጥተን ለመፈጸም ያስችላል ብለዋል።