Author: Samara University

Feb
22

The 2nd Internationa Research Conference on “Leveraging Applied Knowledge for Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities” is running now and will be held for two days from February 22-23/2025.

2ተኛው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ “ተግባራዊ እውቀትን ለአርብቶ አደር እና ከፊል-አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ለውጥ ጥቅም ላይ ማዋል” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል:: በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር ሬዶ የባህል እና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከል የሚካሄደው ይህ ኮንፈረስ ለሁለት ቀናት ከየካቲት 15-16/2017 ዓ.ም ይቆያ::

DETAIL
Feb
22

የጋራ አረዳድን በማስረፅና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው

ሰመራ፤የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፡- የጋራ አረዳድን በማስረፅ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር እና ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ። “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሐሳብ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩን የከፈቱት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሠላምና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ውበቴ ታደገ እንዳሉት፤ “ዘላቂ ሰላም እና አገራዊ መረጋጋት ሊኖር የሚችለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ሲኖር ነው”። እንደ አገር እና ዜጋ የጋራ የሆኑ ህልሞች፣ መገለጫዎች፣ ስጋቶች፣ ጥቅሞችና እሴቶች ያሉን ህዝቦች በመሆናችን የጋራ አረዳድን በማዳበር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ማስረፅ አለብን ብለዋል። ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን ያስገነዘቡት ወይዘሮ ውበቴ፤ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛውን ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር በመሥራት በጋራ ለመልማትና ለማደግ እየሠራች መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ቀጠናዊ ትስስርን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ እንዳለውም አብራርተዋል። በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱራህማን ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው በመድረኩ የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅና ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ይመከራል ብለዋል። በፓናል ውይይቱ ላይም በሠላም ሚኒስቴር የብሔራዊ መግባባት ዴስክ ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁንን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች እንዲሁም እንግዶች ታድመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #Ethiopia

DETAIL
Feb
22

ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር

ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት”በሚል ርዕስ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል:: #ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት_11_ቀን 2017ዓ.ም “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት” በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ሰላም ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል:: የውይይት መነሻ ጥናታዊ ፅሑፍ በመምህር ሀይሌ ረዳ ቀርቦ በሰነዱ ላይ ጥያቄዎች ፣ አስተያየቶች እና ውይይት ተደርገዋል:: የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳን ዶ/ር አብዱረህማን ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው “እንደ ዜጋ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ቀጠናዊ ትስስርን በሚገባ ተረድተን ሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማስፈን በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲናበረክት ለማስገንዘብ የተዘጋጀ መድረክ ነው” ሲሉ ተናግረዋል:: በህ/ተ/ምክር ቤት የሰላም እና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ ወ/ሮ ውበቴ ታደገ ፣ “ዘላቂ ሰላም እና አገራዊ መረጋጋት ሊኖር የሚችለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ሲኖር ነው”። እንደ አገር እና ዜጋ የጋራ የሆኑ ህልሞች፣ መገለጫዎች፣ ስጋቶች፣ ጥቅሞችና እሴቶች ያሉን ህዝቦች በመሆናችን የጋራ አረዳድን በማዳበር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ማስረፅ አለብን” ብለዋል። የተከበሩ አቶ ገዛሀኝ ጥላሁን ፣ በሰላም ሚኒስቴር የብሄራዊ መግባባት ዴስክ ሀላፊ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄዱ ያሉ መሰል ውይይቶች ለእርስበርስ እና ቀጠናዊ መግባባት ብሎም ለጋራ ጥቅሞቻችን መከበር ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል:: በመድረኩ ከሰላም ሚኒስቴር ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና የካውንስል አባላት እንዲሁም መምህራን እና የተማሪ ተወካዮች ተሳትፈዋል::

DETAIL
Feb
22

ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን መሰረታዊ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ስርዓት/GIS ስልጠና እየሰጠ ነው።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት 4/2017 ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመሰረታዊ ጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS) ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና ከሁሉም ትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ ተመራማሪዎች እና መምህራን እየሰጠ ነው። በዚህ ስልጠና መምህራን የጂአይኤስ ሶፍትዌርን ለምርምርም ሆነ ለማስተማር ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ ያለመ በተግባር ላይ የተመሰረተ ስልጠና መሆኑ ተመላክቷል። ስልጠናውን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት ከተከታታይ ሙያዊ ልማት (CPD) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፣ የጂኦሎጂ ፣ የጂኦግራፊ እና የአካባቢ ጥናት መምህራን እያሰለጠኑ እንደሆነ ተገልጿል።

DETAIL
Feb
17

Samara University Enhances Earth Sciences Capabilities with International Collaboration.

#Samara University PR, 10 Feb 2025– In a significant boost to academic collaboration, Samara University’s School of Earth Sciences has received a substantial donation of geological research laboratory materials from two distinguished visiting professors: Dr. Ramon Arrowsmith of Arizona State University and Dr. Erin DiMaggio from Pennsylvania State University.   The donation, comprising books, a microscope,hand lens, grain size chart, and water quality sensor to advance geological research and education at Samara University.   The contribution stems from the professors’ ongoing involvement in the “Ledi Geraru Research Project”, a 25-year multidisciplinary initiative focusing on geology, paleontology, and archaeology in the Afar Region near Mille, Ethiopia.   Rahwa Gebrehiwet, a Samara University staff member at the School of Earth Sciences and active participant in the Ledi Geraru project, played a pivotal role in facilitating the donation.   Dr. Abdurahman Kedir, Vice President of Academic Affairs at Samara University, expressed gratitude for the donation, noting its alignment with the institution’s strategic goals. “Afar is a natural laboratory for earth science, home to landmark discoveries like Lucy, Selam, and Hadar, as well as dynamic geological activity. These materials will empower hands-on learning as we transition into a University of Applied Sciences,”he stated.   He also emphasized the broader implications of the collaboration, which “strengthens ties between SU, ASU, and PSU, paving the way for student and staff exchanges, shared resources, and joint research endeavors.” Last year, Samara University honored Prof. Donald Johanson, discoverer of the Lucy fossil, by naming its College of Social Sciences and Humanities after him during Lucy’s 50th anniversary celebrations.   This latest contribution highlights the growing global recognition of the Afar Region as a critical site for earth sciences research, while positioning Samara University as a hub for applied learning and cross-continental academic collaboration. #we_serve_the _community! Public Relations Executive ✍️ Mohammed Ahmed Abegar 📸 Yared Alemu

DETAIL
Feb
17

ዩኒቨርሲቲው በሲባይቢ ወረዳ ተከስቶ ለነበረው የእንስሳት ወረርሽኝ የህክምና አገልግሎት ምላሽ መስጠቱን ገለፀ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ ጥር_ 30/2017ዓ.ም ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በያንጉዲ ዞን ሲባይቢ ወረዳ አራት ቀበሌዎች ድንገተኛ የእንስሳት ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ ከህብረተሰቡ በቀረበለት ጥያቄ መሰረት ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ቡድን በመላክ የሶስት ቀን ዘመቻ ማድረጉን ገልጿል:: የህክምና ቡድኑ ከወረዳው ግብርናና አርብቶ አደር ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወረርሽኙ በተከሰቱባቸው በኡዴልታ፣ ቴሌ፣ ኡንዳፎዖ እና ቤሎቡሊ ቀበሌዎች 3ሺህ የሚሆኑ እንስሳትን በተሳካ ሁኔታ ማከም  ተችሏል ሲል የህክምና ቡድኑ አስታውቋል።

DETAIL
Feb
17

በዩኒቨርሲቲው የመምህራን ማህበር ጉባኤ እና አዲስ የስራ-አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄዷል::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ጥር_29_2017ዓ.ም በዛሬው እለት በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የመምህራን ማህበር ጉባኤ እና አዲስ የስራ አስፈጻሚዎች ምርጫ ተካሄዷል:: በጉባኤ ላይ ዶ/ር ዩሀንስ በንቲ የኢትዮጲያ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት : ዶ/ር ፈቃዱ ዘለቀ የዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት: ዶ/ር መሀመድ ኡስማን የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንቶች: የኮሌጅና የት/ት ቤት ዲኖች:የት/ት ክፍል ሀላፊዎች እና የማህበሩ አባላት ተገኝተዋል:: በዚህ ምርጫ መሰረት 1. መሀመድ አሊ መሀመድ-የማህበሩ ፕሬዝዳንት 2. ዶ/ር ኢፋ ታደሰ ደበሌ-ም/ፕሬዝዳንት 3. ይባቤ ንጉሴ-ዋና ጸሃፊ 4. ነኢማ ሰይድ-ም/ዋና ጸሃፊ 5. አብዱልከሪም የህያ-ኦድተር 6. እልፍነሽ መዝገቡ-ፋይናንስ ሆነው በደሞክራሲያዊ የምርጫ ሂደት የአብላጫ ድምፅ በማግኘት ተመርጠው ቃለመሃላ ፈፅመዋል:: ይህ አዲስ አደረጃጀት በአጠቃላይ የተቋሙ መምህራንን መብት ማስከበር እና በተቋሙ ውስጥ በመማር ማስተማር ፣ በአስተዳደር ፣ በአቅም ማጎልበት ፣ በትምህርት ጥራት እና ሥነ ምግባር ጉዳዮችን በተደራጀ መልኩ ለመቅረጽ እና ለማንቀሳቀስ የሚያስችል አስተዳደራዊ ለውጥ እንደሚያምጣ አመራሮች እና አባላቱ አስተያየት ሰጥተዋል። ተጋባዥ የመምህራን ማህበር ፕሬዝዳንቶቹ ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለመምህራን ቤት መስሪያ ከሰመራ ሎጊያ ከተማ አስተዳደር እና ከክልል አስተዳደር ተረክቦ ያጠረውን 200ሺ ካ.ሜ ቦታ ጎብኝተዋል። ከፍተኛ አመራሮቹ ለክልሉ እና ከተማ አስተዳደሩ ለመምህራን ላደረገው ቀና ትብብር የላቀ ምስጋና አቅርበዋል:

DETAIL
Feb
17

ዩኒቨርሲቲው የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ስልጠና ሰጠ::

ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የንብረት አስተዳደር ሂደቱን ቀልጣፋ:ተአማኒ እና ብክነትን የሚቀንስ የንብረት አስተዳደር መተግበሪያ ወደ ስራ ማስገባቱን ተከትሎ በተቋሙ ለአራቱም ዘርፍ በየደረጃው ላሉ አመራሮች እና ሰራተኞች ከጥር 26-28 2017ዓ.ም ድረስ የቆየ በንብረት አስተዳደር ስራ-አስፈጻሚ የተዘጋጀ ስልጠና ሰጥቷል:: ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የውስጥ የአሰራር ሂደቱን ቀልጣፋ እና ተአማኒ የሚያደርጉ 10 የሚሆኑ መተግበሪያዎችን በፋይናንስ:በግዥ: በብቃትና ሰው ሀብት: በሬጅስትራር: ፈተናዎች ማዕከል እንዲሁም በሌሎች ክፍሎች በመዘርጋት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል:: ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ የመማር ማስተማር ስራውንም ወደ ኢ-ለርኒንግ ለማስገባት ዘመናዊ መልቲ ሚዲያ ስቱዲዮ አስገንብቶ:መምህራንን እና ተማሪዎችን እያሰለጠነ የሚገኝ ተቋም ነው::

DETAIL