3ኛ ቀን-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የተለያዩ ክንውኖችን አስተናግዷል።
ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት 3ኛ ቀን በተለያዩ መርሃግብሮች ማለትም በፅዳት ዘመቻ፣በጤና ምርመራ ፣እንስሳት ህክምና፣ነፃ የህግ አገልግሎት ክንውኖችን በማካሄድ ቀጥሏል: በዛሬው የፅዳት እና የእፅዋት እንክብካቤ ቀን”ንፁህ እና ምቹ አካባቢ ለተሟላ ጤንነት” በሚል መሪ ሀሳብ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ የከተማ አስተዳደሩ ነዋሪዎች በተገኙበት ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ዋና በር ጀምሮ በዙሪያው ያሉ መንደሮችን የማፅዳት ስራ ተሰርቷል:: በማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር “በኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ)” እግርኳስ ሜዳ ጨዋታዎችን እያስተናገደ ቀጥሏል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ
Health Screening-የደም ግፊት እና የስኳር ልኬት/ምርመራ ተከናውኗል::
ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ29/2017ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት የጤና ሳምንት-3ኛ ቀን ፕሮግራሞች እንደቀጠሉ ናቸው። ትናንት በእጅጉ የተሳካ የደም ልገሳ ተካሂዷል:: በዛሬው የጤና ሳምንት አገልግሎት መርሃ ግብር ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ነፃ የጤና ምርመራ አገልግሎት ማለትም Blood Pressure and Blood Sugar Screening and Counciling ስራ ተከናውኗል:: በተጨማሪም የህክምናና ጤና ሳይንስና ኮሌጅ ባለሙያዎች በሰመራ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ነፃ የጤና ትምህርት እና ምክር አገልግሎቶች በተለይ የግል እና የቡድን ጤና ፣ንፅህና፣አጠባበቅን የተመለከቱ ትምህርቶች ለተማሪዎች እየተሰጡ ነው:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ
በዩኒቨርሲቲው የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ የትውውቅ እና የውይይት ፕሮግራም ተካሄደ::
ሚያዚያ 28/2017ዓ.ም -ዛሬ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የተገኙት የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የዩኒቨርሲቲያቸውን የትምህርት፣ የምርምር እና የማህበረሰብ አገልግሎት ፕሮግራሞች የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ፣መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት የትውውቅ እና የውይይት መርሃግብር ተካሂዷል:: የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ም/ፕሬዝዳንት ኮሌኔል ሰለሞን ባኔ ስለ መከላከያ ቁልፍ ተልዕኮዎች አብራርተው በተለይ አሁን ላይ ዘመኑ በደረሰበት ቴክኖሎጂ ላይ መድረሱ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ ሚናው የጎላ እንደሆነ አብራርተዋል። ሻለቃ ዶ/ር በተለይ ተካ በመከላከያ ዩኒቨርሲቲ የህዝብና አለምአቀፍ ግንኙነት ዳይሬክተር ስለመከላከያ ዩኒቨርሲቲ ከምስረታ ጀምሮ አሁን እስካለበት ቁመና አጠቃላይ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ስላሉት የተለያዩ ዕድሎችም ገለፃ አድርገዋል። የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከተማሪዎች የተነሱ ሲሆን ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቷቸዋል። አሁን ላይ ዩኒቨርሲቲው ባሉት ፕሮግራሞች ተማሪዎች በምርጫቸው ገብተው መማር እንደሚችሉበት እድል ክፍት እንዳደረገ አብራርተዋል። #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ
በዩኒቨርሲቲው አመታዊውን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት ሁለተኛ ቀን “የጤና ቀን” ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ ተካሂዷል።
#ሠመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/2017-የ2017 አመታዊውን የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት “የጤና ቀን” ምክንያት በማድረግ የደም ልገሳ በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ተካሂዷል። በመርሃግብሩ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ኡስማን፣ የአፋር ክልል ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ ያሲን ሀቢብ፣ ምክትል ፕሬዚዳንቶች፣ መካከለኛ አመራሮች፣ ተማሪዎች በተገኙበት የደም ልገሳ ተካሂዷል:: የጤና አገልግሎቶች በተለያዩ የግንዛቤ መፍጠሪያ መርሃግብሮች በትምህርት ቤቶች ሳምንቱን በሙሉ እንደንሚካሄድ ተገልጿል:: የዚሁ የጤና ቀን አካል የሆነው ነፃ የእንስሳት ህክምና እና ጤና አጠባበቅ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃግብሮች እንደሚካሄዱ ተገልጿል::
የቱሪዝም ቀን ከአርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል ጋር ተከብሯል::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ27/2017ዓ.ም-የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መርሃግብሮች ውስጥ አንዱ የቱሪዝም ቀን ሲሆን ፣ ሚያዚያ 27 የሚከበረውን 84ኛውን የኢትዮጵያ አርበኞች የድል መታሰቢያ በዓል ምክንያት በማድረግ በክልሉ በሚገኘው ድንቅ የተፈጥሮ ሀይቅ “ሎማ ሀይቅ” ጉብኝት ተደርጓል:: ሎማ ሀይቅ ከሰመራ በስተሰሜን ምዕራብ አቅጣጫ 30ኪ.ሜ አካባቢ ርቀት ላይ የሚገኝ ለጅኦቱሪዝም አመቺ የሆነ የተወሰነ ፍልውሃም ያለው ሀይቅ መሆኑን የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምድር ትምህርት ቤት የሰጠን መረጃ ያመለክታል::
የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት መካሄድ ጀምሯል።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ27/2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በየአመቱ ለ5 ተከታታይ ቀናት የሚያካሂደው አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት በተለያዩ መርሃግብሮች ዛሬ ተጀምሯል:: በመክፈቻ ፕሮግራሙ ላይ ዶ/ ር መሀመድ ኡስማን (የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት)፣ የእለቱ የክብር እንግዳ አቶ ሀሚድ ዱላ (በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ እና የአፋር ክልል ባህል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ)፣ ከፍተኛ አመራሮች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በተገኙበት የተከፈተው የ2017ዓ.ም አመታዊ የማህበረሰብ አገልግሎት ሳምንት የጤና ስፖርት የእግር ኳስ ውድድር መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ በቅርቡ በድንገተኛ አደጋ በሞት ለተለየን ለወጣቱ የስፖርት ጋዜጠኛ ኑር ሁሴን አሊ(ኑሩ ከዳባ) የህሊና ፀሎት ተደርጓል:: በተጨማሪም ኑር ሁሴን በስፖርቱ ዘርፍ በዩኒቨርሲቲው እግርኳስ ክለብ እና ለክልሉ ስፖርት እድገት ላበረከተው ጉልህ አስተዋጾ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የእግር ኳስ ሜዳ በስሙ ተሰይሟል:: ዛሬ በAdmin እና በCDA-Health College መካከል የተደረገው ጨዋታ አምና ዋንጫ በወሰደው Admin 3ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል:: በዛሬ ከሰአት መርሃ ግብር በAcademic Admin እና College of Engineering and Technology መካከል ጨዋታው የሚቀጥል ይሆናል::
The University Provides Thesis Training to Awash Center Postgraduate Students.
The University Provides Thesis Training to Awash Center Postgraduate Students. ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለአዋሽ ማዕከል የድህረ ምረቃ ተማሪዎቹ በአካዳሚክ ጥናታዊ ፅሁፍ ዝግጅት ላይ ያተኮረ ስልጠና ከሚያዚያ 24-26 ሰጥቷል። #Samara_University_4_May_2025 — Samara University has conducted a comprehensive training session focused on academic thesis preparation for its postgraduate students at the Awash Teaching Center. Held from May 2–4, 2025, the training aimed to equip postgraduate students with the necessary skills and guidance to successfully complete their thesis projects. Located 370 kilometers from the university’s main campus, the Awash Teaching Center was established as part of Samara University’s broader commitment to expanding educational access to the community. And also steadily extended its academic footprint operating teaching campuses in Worer, Bati, Aysaita, Chifra, and Abala, offering undergraduate and graduate programs.
ዩኒቨርሲቲው ሰሞኑን ተከስቶ ለነበረው የፍየል ወረርሽኝ ምላሽ መስጠቱን ገለፀ::
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ/23/2017 ዓ/ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ: የዱብቲ ወረዳ ማህበረሰብ በፍየሎች ላይ ሰሞኑን ለተከሰተው ወረርሽኝ አስቸኳይ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጣቸው ለዩኒቨርሲቲው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ከሚያዚያ 18 እስከ 21/2017 ዓ.ም የተንቀሳቃሽ ህክምና አገልግሎት መስጠቱ ተገልጿል:: ዩኒቨርሲቲው ጥያቄውን ተቀብሎ የሀኪሞች ቡድን በመላክ በጥናት ላይ የተመሰረተ ህክምና በሽዎች ለሚቆጠሩ ፍየሎች እና በጎች በዋድ ባዱራ፤ ቀበሌ 03 እና ሂናሌ ቀበሌዎች ፈጣን ምላሽ ሰጥቷል። የሀኪሞቹ ቡድን ሪፖርት እንደሚያሳየው ከሆነ በቦታው ሲደርሱ 3 ፍየሎች ሙተው 100 የሚሆኑት በከባዱ ታመው ተቅማጥ፣ሳል የአፍንጫ ፍሳሽ እና ሙቀት የሚታይባቸው ፍየሎች ማግኘታቸውንና ማከማቸውን እንድሁም የግንዛቤ ትምህርት መስጠታቸውን ገልጸዋል። በመጨረሻም ባለሙያዎቹ ዩኒቨርሲቲው ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ገልፀው የሚከተሉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ለህብረተሰቡ አስተላልፈዋል:: * የህመም ምልክት ሲያዩ የታመሙትን ከጤናማዎቹ ለይቶ ማቆየት: በተናጥል መመገብ እና በቂ የውሃ መስጠት * አዲስ የሚገቡ ፍየሎችን ከመንጋው ጋር ሳይቀላቀሉ ለሁለት ሳምንታት ለይቶ መከታተል * እንስሳቱ የተለመዱ በሽታዎችን መከላከያ ክትባቶችን መውሰዳቸውን ማረጋገጥ * የበሽታ ስርጭትን ለመቀነስ መጠለያዎችን እና የምግብ እና የውሀ ቦታዎችን አዘውትሮ ማጽዳት:ንፅህናውን መከታተል * የተለዩ ክስተቶችን ሲያዩ በአፋጣኝ ለእንስሳት ህክምና ማእከል/ባለሙያ ሪፖርት ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ አስገንዝበዋል:: #ማህበረሰቡንእናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ