Uncategorized

Apr
16

The University held a Workshop Evaluating Internally Funded Research Projects.

#Samara_University_16April,2025-Samara University hosted a significant workshop to evaluate its internally funded research projects, highlighting innovative solutions to the Region’s socio-economic and environmental challenges. Officially opened by Dr. Mohammed Usman, the university’s president, the event showcased research across key thematic areas including geo-tourism, biotechnology, digital innovation, agriculture, public health, soil science, climate resilience, urban development, and ecological conservation. The workshop emphasized a comprehensive, interdisciplinary approach to regional transformation and reaffirmed the university’s role in advancing evidence-based policymaking and sustainable development both regionally and nationally.

DETAIL
Apr
15

ዩኒቨርሲቲው በሚሌ ወረዳ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት ሰጠ።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ07_2017ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተንቀሳቃሽ የእንስሳት ህክምና አገልግሎት (Mobile Veterinary Service) በሚሌ ወረዳ በተመረጡ ሶስት ቀበሌዎች ሠጥቷል። ለአራት ተከታታይ ቀናት በተሰጠው የህክምና አገልግሎት ከ1ሺ 400 በላይ እንስሳትን የ Parasitism, Systemic Infection and wound ማከም መቻሉን ከሀኪሞች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። የበሽታ መከላከል የህክምና አገልግሎትን በሌሎች አካባቢዎችም ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት ከብሄራዊ የእንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት እና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር እየተደረገ መሆኑን የእንስሳት ህክምናና ሳይንስ ኮሌጅ አሳውቋል። ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

DETAIL
Apr
15

The University Provided Training on Machine Learning with Python.

#SamaraUniversity_PRE_15April2025-Samara University has carried out a three-day training program, “Foundations of Machine Learning with Python,” organized by its Research, Publication, Ethics, and Dissemination Directorate. The training aims to equip faculty with practical, in-demand skills in AI and data science. Organized by the Research, Publication, Ethics, and Dissemination Directorate, the hands-on, in-demand skills in AI and data science; Python-based machine learning applications relevant to fields like healthcare, agriculture, and finance. The training marks a step forward in integrating AI into the university’s academic and research culture. #Weservethecommunity! PublicRelationsExecutive MohammedAhmedAbegar

DETAIL
Apr
14
Apr
14
Apr
14

ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ተገለጸ::

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዚያ05_2017ዓ.ም ኢትዮ ቴሌኮም በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሚማሩ ልዩ ድጋፍ ለሚሹ መደበኛ ተማሪዎች የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ትናንት ባዘጋጀው መድረክ ላይ ገልጿል:: ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት 80 (ወንድ እና ሴት) ተማሪዎችን በመደገፍ በትምህርታቸው የያዙትን አላማና ፍላጎታቸውን እንዲያሳኩ የሚያግዝ የገንዘብ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጾ: በቀጣይ በቁሳቁስም ድጋፉን አጠናክሮ የመቀጠል እቅድ እንዳለው አስታውቋል ። በመድረኩ ተማሪዎች የኢትዮ ቴሌኮምን አገልግሎቶች በብቃት ለመጠቀም በሚያስችሉ ክህሎቶች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል:: ይህም ለተማሪዎች አስፈላጊ ግብአቶችን ከማሟላት ባለፈ የኢትዮ ቴሌኮም አምባሳደር እንዲሆኑ የሚያነሳሳ የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች የማስተዋወቅ ስራ ሰርቷል። ሠመራ ዩኒቨርሲቲ: ኢትዮ ቴሌኮም ለተማሪዎች እያደረገው ላለው ድጋፍ ምስጋናውን እየገለፀ: ይህን ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ በማድረስ ተማሪዎችን እና ማህበረሰቡን የሚጠቅም ምቹ የመማር ማስተማር ሁኔታን መፍጠር እንደሚቻል ያምናል። ኢትዮ ቴሌኮም ከሰመራ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለአመታት በአጋርነት እየሰራ ያለ ድርጅት መሆኑም ተመላክቷል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታላቅ የስነ-ፅሁፍ ምሽት አካሄዱ::

በርካታ የጥበብ አፍቃሪያን መምህራን:ሠራተኞች እና ተማሪዎች የታደሙበት መድረክ ‎ላይ ቲያትር ግጥም: ሞኖሎግ: ሙዚቃ:ዳንስ እና የጭውውት ትዕይንቶች ቀርበውበታል:: የዩኒቨርሲቲው “ድንቅ የተማሪዎች ክበብ” አባላት ዘወትር ቅዳሜ “አንድ ቀን ለራሴ “በሚል መርሀግብር የተለያዮ ፕሮግራሞችን በማቅረብ የሚታወቁ ሲሆን ከታዋቂ የስነ-ጥበብ ባለሙያ ጋር በመስራት ከ500 ሰው በላይ የተኘበት የጥበብ ምሽት ሲያዘጋጁ የዛሬው የመጀመሪያቸው ነው:: ተማሪዎቹ በስነ-ፅሁፍ እያዝናኑ ቁም ነገር የሚያስጨብጡ ሀሳቦችን በማንሳት መድረኩን ከማድመቅም ባለፈ የመማር ማስተማሩን እና የተማሪዎችን የግቢ ቆይታ አይረሴ የሚያደርጉ የጥበብ ስራዎችን በማቅረብ ቀልብ መግዛት መቻላቸውን የታዳሚው ቁጥር ምስክር ነው:: ምሽቱ ከስነ-ፅሁፍ ስራዎች በተጨማሪ:በሀገር አቀፉ የመላው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል ላይ ለተሳተፉ የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልኡክ በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ስፖርት ማህበር እና በአዘጋጁ የአድስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀ የምስክር ወረቀት ተበርክቷል:: በተለያዩ ጊዜያት በተማሪዎች አቀባበል ላይ ተሳትፎ ላደረጉ አካላትም እውቅና ተሰጥቷል::በመጨረሻም የእለቱን የስነ-ፅሁፍ ምሽት ላዘጋጁት:ላስተባበሩት እና በትወና ላደመቁት ተማሪዎች ምስጋናና እውቅና በመስጠት ተጠናቋል:: #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL
Apr
14

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “የምስለ-ችሎት ዉድድር” አካሄዱ።

#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_ሚያዝያ_03_2017 ዓ.ም-በሰመራ ዩኒቨርሲቲ ህግ እና ስነ መንግስት ትምህርት ቤት: የህግ ተማሪዎች “የምስለ-ፍርድ ቤት ዉድድር” በርካታ ታዳሚዎች በተገኙበት አካሒደዋል። የምስለ-ችሎት ውድድር በዩኒቨርሲቲዎች ደረጃ እንዲሁም በሀገር አቀፍ እና አለም አቀፍ ደረጃ የሚዘጋጅ ሲሆን:ተማሪዎች በፅንሰ ሀሳብ የተማሩትን በተግባር የሚለማመዱበት መድረክ በመሆኑ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ውድድሩን የዳኙት መምህራን ተናግረዋል:: ተወዳዳሪ ተማሪዎቹ ዩኒቨርሲቲያቸውን ወክለው በቅርቡ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የህግ ተማሪዎች ምስለ-ችሎት ውድድር ስለሚሳተፉ: የዛሬው ምስለ ችሎት ለቅድመ ዝግጅት ይረዳቸው ዘንድ የተዘጋጀ መሆኑን ትምህርት ቤቱ ገልጿል። #ማህበረሰቡን_እናገለግላለን! መሀመድ አህመድ አበጋር ያሬድ አለሙ የህዝብ ግንኙነት ስራ-አስፈፃሚ

DETAIL