በአካባቢ ስሙ ‘አስኤራ’ ወይም ‘አስኤራይቶ (As-era/ As-erayto) በሳይንሳዊ ስሙ (Dracaena ombet) በመባል ይታወቃል::
በአካባቢ ስሙ ‘አስኤራ’ ወይም ‘አስኤራይቶ (As-era/ As-erayto) በሳይንሳዊ ስሙ (Dracaena ombet) በመባል ይታወቃል:: በአፋር ክልል ውስጥ ከሚገኙ በርካታ ሀገር በቀል ዛፎች ውስጥ አንዱ እንደሆነ ይነገራል:: በአሁኑ ሰአት የዚህ ዛፍ ዝርያ በመመናመን ላይ እንደሚገኝ ጥናቶች ይጠቁማሉ:: በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ህይወት ትምህርት ክፍል መምህር እና የሶስተኛ ዲግሪያቸውን በእፅዋት ሳይንስ ዘርፍ በመከታተል ላይ የሚገኙት መ/ር መሀመድ ሹምባህሪ ጋር ያደረግነውን ቆይታ እንደሚከተለው እናቀርባለን:: #ሠዩ:-በቅድሚያ ለዚህ ቃለ-መጠይቅ ፈቃደኛ ሆነው ሙያዊ ትንታኔ ለመስጠት ስለመጡ አመሰግናለሁ:: #መሀመድ:- እኔም አመሰግናለሁ:: #ሠዩ:- ባለፈው ሳምንት እርሶ ከሌሎች ተመራማሪዎች ጋር በጋራ የሰራችሁት የምርምር ስራ በፈረንጆች አቆጣጠር 16 April 2025 መታተሙን ተመልክቻለሁ። እስኪ ስለ እትሙ ትንሽ ይንገሩኝ? #መሀመድ:-አስኤራን በተመለከተ በዋናነት ጥናት እየሰራሁ ያለሁ ቢሆንም ፣ ጥሩ የምርምር ውጤት እንዲሆን ከሌሎች ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት publication ላይ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በቀላሉ በማለፍ ይህ ምርምር ፣ Springer Nature በተባለ አለም አቀፍ ጆርናል ፣ የ Biodiversity and Conservation አምድ ላይ “Dracaena ombet in peril in Ethiopia: a call for attention and action” በሚል ርዕስ ማሳተም ችለናል። ለዚህም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ጥናታዊ ፅሁፍ ላይ አብረውኝ በመስራት የተሳተፉትን ተመራማሪዎችን ሁሉንም አመሰግናቸዋለሁ። #ሠዩ:- እስኪ ስለ አስኤራ ዛፍ ምንነት እና ጥቅሞቹን ይግለፁልኝ? #መሀመድ:- የአስኤራ ዛፍ ድርቅን የመቋቋም ችሎታ ያለው ፣ ቅጠሉን እንስሳት ይመገቡታ ፣ ፍሬውን ደግሞ ሰዎች ለምግብነት እንደሚጠቀሙት እንዲሁም ለመድሀኒትነት ይውላል:: የአስኤራ ግንዱ ለቤት እቃዎች ማለትም ለወተት ማለቢያ ፣ ለአይብና ቅቤ መያዣ ፣ ለገንፎ ማቅረቢያ ፣ ለንብ ቀፎ መስሪያነት እንዲሁም በስሩ ከፀሀይ ተከልሎ አረፍ ለማለት የሚጠቅም አይነተኛ የደረቃማና የህፀተ-ዝናብ አካባቢ ዛፍ ነው:: #ሠዩ:- የአስኤራይቶ ዛፍ ከኢትዮጵያ ውጭ እና በሀገራችን እና የት የት አካባቢ ይገኛል ፣ በምን ሁኔታ? #መሀመድ:- በአሁኑ ሰዓት አስኤራ ከኢትዮጵያ ውጪ በግብፅ ፣ ሱዳን እና የመን የሚገኝ ሲሆን ፣ እፅዋቱ በከፋ ደረጃ እየተመናመነ በመሆኑ IUCN በአለም አቀፍ ደረጃ አደጋ ላይ ያለ እፅዋት በሚል ተርታ አሰለፎት የሚገኝ የእፅዋት ዝርያ ነው። አስኤራይቶ እስከ አሁን በተደረጉ ጥናቶች በኢትዮጵያ ውስጥ በአፋር ክልል ፣ በትግራይ ክልል አንዳንድ ቦታዎች እና በሶማሌ ክልል እንደሚገኝ አመላክተዋል። በተለያዩ የተፈጥሮና ሰው-ሰራሽ ምክንያቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ ቁጥሩ በመመናመን ላይ የሚገኝ ተክል ነው። #ሠዩ:- የሰራችሁት ጥናት አስኤራይቶን ለመታደግ ምን አስተዋጽዖ ይኖረዋል ብለው ያስባሉ? #መሀመድ:- አሁን Springer Nature ላይ ታትሞ በወጣው ጥናት ላይ ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ እኔን ጨምሮ የመቀሌ፣ የአድግራት ዩኒቨርሲቲዎች እና የፐኢለኢም ኢትዮጵያ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ነው:: በጥናቱ እፅዋቱ ያለበትን ደረጃ እና መታደግ የሚቻልባቸውን ምክረ ሀሳቦች ጭምር አስቀምጠናል:: ከዚህ በተጨማሪም የተለያዩ ጥናቶች በመቀሌ፣ በአዲስ አበባ፣ በአዲግራት እና በሠመራ ዩኒቨርሲቲዎች የተከናወኑ እና በመከናወን ያሉ ሳይንሳዊ ጥናቶች እፅዋቱን መታደግ አስፈላጊ እና ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑን ይጠቁማሉ። #ሠዩ:- አስኤራይቶንም ሆነ ሌሎች በመመናመን ላይ ያሉ ሀገር በቀል እፅዋቶች ለመታደግ እንደ ዩኒቨርሲቲ ምን እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው? #መሀመድ:- ጥናቶችን መሠረት በማድረግ በሰመራ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት ስር የተቋቋመ የደረቃማ አካባቢ ብዝኃ-ህይወት ምርምር: ልማትና ጥበቃ ማዕከል ተቋቁሟል:: ይህም በተቋማችን ዋናው ግቢ ውስጥ ለሀገር በቀል ዛፎች ማዕከልነት የሚውል ቦታ በመረከብ ከክልሉ የተለያዩ ወረዳዎች የእፅዋት ዘር እና ቡቃያ በማሰባሰብ ቦታውን የማልማት ስራ ለመጀመር ዝግጅቱ ተጠናቋል:: ይህንንም ማዕከል እኔ በሀላፊነት እያስተባበርኩ እገኛለሁ። በማእከሉ ለማልማት ከታቀዱ ሀገር በቀል ዛፎች ውስጥ አስኤራ ይገኝበታል። ማዕከሉ የመማር ማስተማር እና የምርምር ማዕከል ከመሆን ባሻገር ለአካባቢው ማህበረሰብ የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ይሆናል። በተጨማሪም ሀገር በቀል ዛፎችን ችግኝ በማፍላት ለህብረተሰቡ የማከፋፈል እቅድም ተይዟል:: በዚህ በኩል ሀሳቡን በመደገፍ ስራውን በማስቀጠል ከግብ ለማድረስ ላለው ተነሳሽነት የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራር ምስጋና ይገባቸዋል:: #ሠዩ:- እጩ ዶ/ር መሀመድ ሹምባህሪ የአስኤራይቶ እፅዋትን አስመልክቶ ለሰጡን ሰፋ ያለ ሙያዊ ትንታኔ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ስም አመሰግናለሁ:: ውድ አንባቢያን በዛሬው ዘገባችን በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ህይወት ትምህርት ክፍል መምህር እና የሶስተኛ ዲግሪ በእፅዋት ሳይንስ ዘርፍ በመከታተል ላይ ከሚገኙት መ/ር መሀመድ ሹምባህሪ ጋር ያደረግነው ቆይታ ይህን ይመስል ነበር:: ይህን ፕሮግራም በማዘጋጀት ወደ እናንተ ያቀረብኩት እኔ #መሀመድ_አህመድ_አበጋር ከህዝብ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ ነው:: በሌላ ምንባብ እስከምንገናኝ ሰላም ለሁሉም! #Happy_Earth_Day! N.B:-ይህ የአስኤራ ፎቶ የተነሳው በኢረብቲ-አብአላ መንገድ የአዱ ተራራ አካባቢ ነው።
The University Establishes International Advisory Board for One of Its Areas of Excellence.
Samara_University_PRE,Feb-24/2025 – In a significant step towards enhancing tourism education, Samara University has officially established an International Advisory Board for its School of Tourism and Hospitality Management (SoTHM). The board comprises distinguished founding members, including His Excellency Sileshi Girma, the State Minister of Tourism and Board Chairman of Samara University; Dr. Mohammed Usman, President of Samara University; Mr. Ebrahim Humed, Head of the Afar Regional State Tourism Bureau, Dr. Abdurahman Kedir, Academic Affairs V/President of Samara University, Dr. Jason Willis Michael Kelly from the Hong Kong Polytechnic University’s SoTHM; and Dr. Abraha Haftom, Dean of SoTHM at Samara University. The board’s expertise is expected to provide strategic guidance, share best practices, and facilitate international collaborations, contributing to a curriculum that adheres to global standards and prepares students for the dynamic tourism industry. This initiative will benefit both the regional and national tourism sectors while promoting sustainable economic development. we serve_the Community! ✍️ By Mohammed Ahmed📸 Yared AlemuPublic Relations Executiveለአዳድስ ተቋማዊ መረጃዎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን አባል ይሁኑ!ፌስቡክ👇https://www.facebook.com/susamara2008/ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopiaዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1ዌብሳይት👇Www.su.edu.etትዊተር👇https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09ሊንክድን👇https://www.linkedin.com/company/semara-university/ቲክቶክ👇https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1
በስኬት_ተጠናቀቀ_Successfully_Concluded.
The 2nd Internationa Research Conference on “Leveraging Applied Knowledge for Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities” held from February 22-23/2025 has successfully concluded. ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የቆየው 2ተኛው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ ተጠናቋል:: ሠመራ ዩኒቨርሲቲ የካቲት 17/2017 ዓ.ም-በሠመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት ሲካሄድ የነበረው 2ተኛው አለምአቀፍ የምርምር ኮንፈረንስ በስኬት ተጠናቋል:: ኮንፈረንሱ “ተግባራዊ እውቀትን ለአርብቶ አደር እና ከፊል-አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ለውጥ ጥቅም ላይ ማዋል” በሚል ርዕስ ነበር:: 24 የምርምር ውጤቶች የቀረቡበት እና ከአውሮፓ -ጣሊያን፣ ከኤሲያ-ቻይና፣ከአፍሪካ-ኬንያ እንዲሁም ከካናዳ እና ከሀገራችን የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ምሁራን እና ከፌደራል እና ክልል መንግስት ተጋባዥ እንግዶችን ያሳተፈው 2ተኛው አለምአቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል:: በኮንፈረንሱ መክፈቻ ላይ ቁልፍ መልዕክት ያስተላለፉት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት፣ ስራ ስምሪትና የቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዶ/ር ነገሬ ሌንጮ:በአፋር ክልል ያሉ ብዝሀ የተፈጥሮ ሀብቶችን በጥናትና ምርምር በመደገፍ ጥቅም ላይ ማዋል አስተዋፅኦው የጎላ ነው ያሉ ሲሆን ሀገራዊ እና ነባራዊ ችግሮችን ለመፍታት መፍትሄ የሚሆኑ ጥናትና ምርምሮች መሰራታቸው የሚበረታታም እንደሆነ ገልጸዋል። የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር መሀመድ ዑስማን በመዝጊያ ንግግራቸው እንደ አፋር ላሉ በረሃማና ከፊል በረሃማ አካባቢዎች ዘላቂ ልማት ለማምጣት የምሁራን ትጋት የጥናትና ምርምር ስራዎቻቸውን ወሳኝ በሆኑ ፖሊሲዎች ማካተት መቀጠል የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡ በኮንፈረንሱ የቀረቡ የቱሪዝም: የግብርና:የስነ-ምድር:ስነ-ህይወት እና የሰብአዊ መብት ጥናቶችን በተመለከተ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ጥያቄዎችን ተመራማሪዎቹ ምላሽ በመስጠት ሁሉንም ያሳተፈ ኮንፈረንስ ተካሄዷል። በኮንፍረንንሱ የቀረቡ የጥናትና ምርምር ስራዎች ለበርካታ ማህበራዊና፣ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች መፍትሄ ጠቋሚ ምክረ-ሃሳቦች የተመላከቱበት ከመሆኑም በተጨማሪ አርብቶ አደሩንና ከፊል አርብቶ አደሩን ማህበረብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ” ባለ 10 ነጥብ የፖሊሲ ምክረሃሳብ/Policy Brief የተሰጠበት ነበር:: በኮንፍረንሱ መዝጊያ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የሰመራ ሎጊያ አስተዳደር ከንቲባ፣ እና የሰመራ ዩዩኒቨርሲቲ የቦርድ አባል አቶ አብዱ ሙሳ እንደተናገሩት ‘የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ እና የክልሉን ፀጋ ተኮር የሆኑ ምርምሮችን በመስራት የጀመረው በጎ ጥረት መቀጠል እንዳለበት አመልክተው ከተለያዩ ቦታዎች የዩኒቨርሲቲውን ጥሪ አክብረው ለመጡ ተመራማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል። የሰመራ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ቀናት በተደረገው 2ተኛው አለም አቀፍ የምርምር ኮንፍረንስ ላይ ለተሳተፉ ተጋባዥ እንግዶች እና ጥናት አቅራቢ ተመራማሪዎች የምስጋና የምስክት ወረቀት ሰጥቷል።
The 2nd International Conference on Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities Launched at Samara University.
February,22,Samara, Ethiopia – The 2nd International Conference on “Leveraging Applied Knowledge for Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities” officially commenced at Samara University. This two-day event, running from February 22-23, 2025, brings together a diverse group of scholars, stakeholders, and government officials from Ethiopia and around the world. The conference aims to foster meaningful discussions and presentations focused on innovative solutions for pastoral and agro-pastoral communities. Attendees include representatives from Ethiopian public universities, federal and regional government officials, experts, and members of the Samara University community. During the opening session, Dr. Mohammed Usman, President of Samara University, delivered a welcoming address, emphasizing the university’s commitment to research initiatives on excellence areas that benefit pastoral and agro-pastoral communities ensuring communities reap tangible benefits. H.E. Dr. Negere Lencho, Chairperson of the Standing Committee on Human Resources, Employment, and Technology Affairs of the House of People’s Representatives, delivered the keynote speech. He highlighted the importance of research in harnessing the diverse natural resources of the Afar region, asserting that “Research and innovation play a pivotal role in unlocking these resources for practical use.” Following the opening speeches, the conference featured presentations of four studies. In the afternoon session continued with eight additional presentations divided into two groups, focusing on discussions aimed at providing insights for policymakers. In total, the conference will showcase 24 studies over two days, with presentations scheduled for both morning and afternoon sessions. The emphasis remains on the critical role of research and innovation in advancing the development of pastoral and agro-pastoral communities, ensuring sustainable benefits for the people. Experts from Europe, Asia, Africa, and various Ethiopian universities are participating, fostering collaborative discussions and research presentations aimed at driving impactful change in these vital areas. Those interested can join us for today’s session in person or via our social media links. we serve_the Community! ✍️ Public Relations Executiveለአዳድስ ተቋማዊ መረጃዎች የማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንን አባል ይሁኑ!ፌስቡክ👇https://www.facebook.com/susamara2008/ቴሌግራም👇 https://t.me/SamaraUniversityEthiopiaዩትዩብ👇 https://youtube.com/channel/UCvDWGawVYKQa_FJY8supkBA?sub_confirmation=1ዌብሳይት👇Www.su.edu.etትዊተር👇https://twitter.com/SamaraunivEthio?t=QlDpWx8vlY_udWdGAztwvg&s=09ሊንክድን👇https://www.linkedin.com/company/semara-university/ቲክቶክ👇https://www.tiktok.com/@samara.university?_t=8ipUGAsrMwg&_r=1
The 2nd Internationa Research Conference on “Leveraging Applied Knowledge for Transformative Change in Pastoral and Agro-Pastoral Communities” is running now and will be held for two days from February 22-23/2025.
2ተኛው አለምአቀፍ ኮንፈረንስ በሠመራ ዩኒቨርሲቲ “ተግባራዊ እውቀትን ለአርብቶ አደር እና ከፊል-አርብቶ አደር ማህበረሰቦች ለውጥ ጥቅም ላይ ማዋል” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ይገኛል:: በሠመራ ዩኒቨርሲቲ በዶ/ር ሬዶ የባህል እና ሀገር በቀል ጥናቶች ማዕከል የሚካሄደው ይህ ኮንፈረስ ለሁለት ቀናት ከየካቲት 15-16/2017 ዓ.ም ይቆያ::
የጋራ አረዳድን በማስረፅና ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ ነው
ሰመራ፤የካቲት 11/2017 (ኢዜአ)፡- የጋራ አረዳድን በማስረፅ ብሔራዊ ጥቅምን በማስከበር እና ቀጣናዊ ትስስርን በማጠናከር ረገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ። “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የህዝቦች ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ሐሳብ የሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው። የውይይት መድረኩን የከፈቱት በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሠላምና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል ወይዘሮ ውበቴ ታደገ እንዳሉት፤ “ዘላቂ ሰላም እና አገራዊ መረጋጋት ሊኖር የሚችለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ሲኖር ነው”። እንደ አገር እና ዜጋ የጋራ የሆኑ ህልሞች፣ መገለጫዎች፣ ስጋቶች፣ ጥቅሞችና እሴቶች ያሉን ህዝቦች በመሆናችን የጋራ አረዳድን በማዳበር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ማስረፅ አለብን ብለዋል። ብሔራዊ ጥቅምን ማስጠበቅ የእያንዳንዱ ዜጋ ሃላፊነት መሆኑን ያስገነዘቡት ወይዘሮ ውበቴ፤ በተለይም የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከፍተኛውን ሚና መጫወት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። ኢትዮጵያ ከአፍሪካ አገራት ጋር በትብብር በመሥራት በጋራ ለመልማትና ለማደግ እየሠራች መሆኑን ጠቅሰው፤ ይህም ቀጠናዊ ትስስርን በማጎልበት የህዝብን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የጎላ ፋይዳ እንዳለውም አብራርተዋል። በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት አብዱራህማን ከድር (ዶ/ር) በበኩላቸው በመድረኩ የአገራችንን ብሔራዊ ጥቅሞች ማስጠበቅና ማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ይመከራል ብለዋል። በፓናል ውይይቱ ላይም በሠላም ሚኒስቴር የብሔራዊ መግባባት ዴስክ ኃላፊ አቶ ገዛኸኝ ጥላሁንን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲው መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች እንዲሁም እንግዶች ታድመዋል። #Ethiopian_News_Agency #ኢዜአ #Ethiopia
ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር
ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት”በሚል ርዕስ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል:: #ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት_11_ቀን 2017ዓ.ም “ብሔራዊ ጥቅሞቻችንና ቀጠናዊ ትስስር ለሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነት” በሰመራ ዩኒቨርሲቲ እና ሰላም ሚኒስቴር ትብብር የተዘጋጀ ሀገራዊ የምክክር መድረክ ተካሄዷል:: የውይይት መነሻ ጥናታዊ ፅሑፍ በመምህር ሀይሌ ረዳ ቀርቦ በሰነዱ ላይ ጥያቄዎች ፣ አስተያየቶች እና ውይይት ተደርገዋል:: የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የአካደሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳን ዶ/ር አብዱረህማን ከድር በመክፈቻ ንግግራቸው “እንደ ዜጋ ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን እና ቀጠናዊ ትስስርን በሚገባ ተረድተን ሚዛናዊ የሕዝቦች ተጠቃሚነትን ለማስፈን በሚያስፈልገው ሁሉ እንዲናበረክት ለማስገንዘብ የተዘጋጀ መድረክ ነው” ሲሉ ተናግረዋል:: በህ/ተ/ምክር ቤት የሰላም እና የውጭ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል የተከበሩ ወ/ሮ ውበቴ ታደገ ፣ “ዘላቂ ሰላም እና አገራዊ መረጋጋት ሊኖር የሚችለው በጋራ ጉዳዮች ላይ ተቀራራቢ ግንዛቤ ሲኖር ነው”። እንደ አገር እና ዜጋ የጋራ የሆኑ ህልሞች፣ መገለጫዎች፣ ስጋቶች፣ ጥቅሞችና እሴቶች ያሉን ህዝቦች በመሆናችን የጋራ አረዳድን በማዳበር ብሔራዊ ጥቅሞቻችንን በእያንዳንዱ ዜጋ ውስጥ ማስረፅ አለብን” ብለዋል። የተከበሩ አቶ ገዛሀኝ ጥላሁን ፣ በሰላም ሚኒስቴር የብሄራዊ መግባባት ዴስክ ሀላፊ በሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች እየተካሄዱ ያሉ መሰል ውይይቶች ለእርስበርስ እና ቀጠናዊ መግባባት ብሎም ለጋራ ጥቅሞቻችን መከበር ወሳኝ ሚና ይኖራቸዋል ብለዋል:: በመድረኩ ከሰላም ሚኒስቴር ፣ ከህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከሠመራ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች እና የካውንስል አባላት እንዲሁም መምህራን እና የተማሪ ተወካዮች ተሳትፈዋል::
ዩኒቨርሲቲው ለመምህራን መሰረታዊ የጂኦግራፊያዊ መረጃ ስርዓት/GIS ስልጠና እየሰጠ ነው።
#ሰመራ_ዩኒቨርሲቲ_የካቲት 4/2017 ዓ.ም-ሰመራ ዩኒቨርሲቲ በመሰረታዊ ጂኦግራፊያዊ መረጃ ሥርዓት (GIS) ላይ የተዘጋጀ ሥልጠና ከሁሉም ትምህርት ክፍሎች ለተውጣጡ ተመራማሪዎች እና መምህራን እየሰጠ ነው። በዚህ ስልጠና መምህራን የጂአይኤስ ሶፍትዌርን ለምርምርም ሆነ ለማስተማር ውጤታማ በሆነ መንገድ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችሉ ያላቸውን ክህሎት ለማሳደግ ያለመ በተግባር ላይ የተመሰረተ ስልጠና መሆኑ ተመላክቷል። ስልጠናውን የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ጽህፈት ቤት ከተከታታይ ሙያዊ ልማት (CPD) ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ሲሆን፣ የጂኦሎጂ ፣ የጂኦግራፊ እና የአካባቢ ጥናት መምህራን እያሰለጠኑ እንደሆነ ተገልጿል።