የህግ ትምህርት ቤቱ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጋር በመተባበር ሥልጠና:ክርክር እና ፊርማ አካሄደ፡፡

የህግ ትምህርት ቤቱ ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጋር በመተባበር ሥልጠና:ክርክር እና ፊርማ አካሄደ፡፡

የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጋር በመተባበር ሥልጠና እና በተማሪዎች መካከል ክርክር እንድሁም የመግባቢያ የስምምነት ሰነድ ፊርማ አካሂዷል፡፡

ሥልጠናው ለሁለት ቀን ከህዳር 28-29/2016 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን”Basic Human Rights, Gender Equality and Human Rights Advocacy” ከህግ እና ማህበራዊ ሳይንስ ለተውጣጡ ተማሪዎች መሆኑ ተገልጿል፡፡ 

ሥልጠናውን በተግባር ለማጠናከር ተማሪዎቹ ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ መብት ላይ ባተኮረ የመከራከሪያ ርዕስ ላይ መምህራን እና ተማሪዎች በተገኙበት ሰፋ ያለ ክርክር አድርገዋል፡፡

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ወ/ም/ፕሬዝዳንት አቶ አደም አሊ ክርክሩ ለተማሪዎች የሃሳብ ፍጭት እንዲያደርጉ፣ የህግ እውቀታቸውን እና የመናገር ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ ያግዛል ሲሉ ገልፀዋል። 


በመጨረሻም የሰመራ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት  ከኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ የተፈራረሙ ሲሆን በሰነዱ መሰረት ከተለያዩ ት/ርት ክፍሎች በተውጣጡ  ተማሪዎች የሰብአዊ መብቶች ክለብ አቋቁመዋል::

ክለቡም የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ ማስጨበጥ፣ ነፃ ክርክር እና የፓናል ውይይት በማካሄድ በህብረተሰቡ እና በግቢው ማህበረሰብ የሰብአዊ መብቶች ግንዛቤ መፍጠር እንዲችል በማለም የተመሰረተ ነው።

=================

ማህበረሰቡን እናገለግላለን!!!

የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ

Leave a Reply

Your email address will not be published.